ዓለም አቀፋዊ አጋርነት እና ትብብርን ለማጠናከር የፖለቲካ ቁርጠኝነት በጣም አስፈላጊ ነው – ክቡር ሚኒስትር ድኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ
________________________________________________
( ሰኔ 28 ቀን 2015ዓ.ም ) በክቡር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን አዘርባጃን ባኩ ከተማ እየተካሄደ ባለው የገለልተኛ አገራት ንቅናቄ ( ናም) የሚኒስትሮች ጉባኤ እየተሳተፈ ነው ::
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የንቅናቄውን የሚኒስትሮች ስብሰባ እያካሄድን ያለነው አለማችን ውስብስብ በርካታ ፈተናዎች በተጋረጠበት በዚህ ወቅት መሆኑን ገልፀው ፤ እርስ በእርስ በተሳሰሩ ዘርፈ ብዙ ቀውስ ወቅት፣ እንደተለመደው ሳይሆን አዲስ እይታ እና ሀሳቦች ያስፈልጉናል ብለዋል።
በተጨማሪም ዓለም አቀፋዊ አጋርነቶችን እና ትብብርን ለማጠናከር የፖለቲካ ቁርጠኝነት በጣም አስፈላጊ እንደሆነ ገልፀዋል ።የአዘርባጃን ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ክቡር ኢልሃም አሊዬቭ በጉባኤው የናም አዘርባጃን ሊቀመንበርነት በ”ባንዱንግ መርሆዎች” መሰረት ፍትህን እና አለም አቀፍ ህግን እና የአባል ሀገራትን ህጋዊ ጥቅም አስጠብቋል ብለዋል። ክቡር ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ሰላም የሰፈነበት እና የበለጸገ ዓለም ለመፍጠር የጋራ ቃል ኪዳናችን አሁን ያለውን ዓለም አቀፋዊ የኢኮኖሚና የፋይናንስ ሥርዓት ካልተሻሻለ ተግባራዊ ሊሆን አይችልም ብለዋል። በመሆኑም አለም አቀፍ የፋይናንስ ስርዓት እንዲሻሻል ጠይቀዋል ።
አምባሳር ምስጋኑ በአየር ንብረት ለዉጥ ኢትዩጵያ ተግባራዊ ያደረገችዉን የአረንጓዴ ልማት፣ ኢትዩጵያ በሰላም ማስከበር የተጫወተችዉን ሚና በጉባኤው ገልፀዋል ።ኢትዮጵያ የገለልተኛ አገራት መስራች አባል እንደመሆኗ የወደፊት ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ የሚያስችል መርህ ላይ ያተኮረ እና ውጤታማ የባለብዙወገን ተሳትፎ ለማድረግ ቁርጠኛ አቋም እንዳላትም ተገልፆል ።
2