በጄዳ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አመራሮች ምርጫ፤
 
በጄዳና አካባቢው የተለያዩ አደረጃጀቶች የተውጣጡ እጩ አመራሮች ሰኔ 09 ቀን 2015 ዓ.ም. በጄዳ ቆንስላ ጄነራል ጽ/ቤት በመገናኘት በቀጣይ ሁለት ዓመታት ኮሙኒቲውን የማስተባበር ሥራ የሚሰሩ ዘጠኝ አባላት ያሉት የሥራ አስፈፃሚ ምርጫ ተካሂዷል።
 
በዚሁ መሰረት ከተለያዩ አደረጃጀቶች ተመርጠው ከመጡ 22 አባላት መካከል 9 የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ተመርጠዋል። ሥራ አስፈፃሚ አባላቱም ሰብሳቢ፣ ም/ሰብሳቢ፣ ፀሐፊ፣ ሂሳብ ሹም፣ ገንዘብ ያዥ፣ የማህበራዊ ጉዳይ ሃላፊ፣ የዜጐች ክትትል ሃላፊና ሁለት አባላት ያሉት የኢንስፔክሽን ኮሚቴ አባላት መርጠዋል።
 
በዚሁ መሠረት አቶ ጀማል ዳዲ ሰብሳቢ፣ አቶ ሲይድ መሀመድም/ሰብሳቢ፣ አቶ መሀመድ ሲራጅ ፀሀፊ፣ ወ/ሮ ሙኒራ ጅሃር ሂሣብ ሹም፣ ወ/ሮ ሙሉወርቅ ነጋሽ ገንዘብ ያዥ፣ አቶ ፈሪድ ሸሪፍ ማህበራዊ ጉዳይ ሃላፊ፣ አቶ ሙሳ ሀሰን ዜጐች ክትትል ሃላፊ፣ አቶ ሚካኤል አጽበሃ የኢንሰፔክሽን ሰብሳቢ እና አቶ አብደላ አማን የኢንሰፔክሽን ፀሐፊ በመሆን ተመርጠዋል።
 
 
 
 
 
 
 
 

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram