በጄዳና አካባቢዋ ከሚኖሩ የተለያዩ የዳያስፖራ አደረጃጀት አመራሮች ጋር ውይይት ተካሄደ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካከለኛው ምስራቅ እና ኤዥያና ኦሺንያ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄነራል ክቡር አምባሳደር ገበየሁ ጋንጋ፣ የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄነራል ክቡር አምባሳደር ሲራጅ ረሺድ እንዲሁም የጄዳ ቆንስላ ጄነራል የሆኑት ክቡር አምባሳደር ሙሉጌታ ከሊል እና ዲኘሎማቶች በተገኙበት በጄዳና አካባቢዋ ከሚኖሩ የተለያዩ የዳያስፖራ አደረጃጀት አመራሮች ጋር ሰኔ 08 ቀን 2015 ዓ.ም. ውይይት ተደርጓል። በውይይቱ ላይ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች፣ የዜጐችን መብትና ጥቅም ከማስጠበቅ አንፃር፣ የዳያስፖራ አደረጃጀቶችን ከማጠናከር እና በቀጣይ በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።የስብሰባው ተሳታፊዎችም በተነሱት ሃሳቦች ላይ ጥያቄና አስተያየት የሰጡ ሲሆን በተነሱት ሃሳቦች ላይ ሰፊ ማብራሪያና ገለፃ ተሰጥቶባቸዋል። 1 Post navigation Joint Statement by the Ministry of Foreign Affairs of the Federal Democratic Republic of Ethiopia and USAID በጄዳ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አመራሮች ምርጫ፤