127ኛው የአድዋ ድል በዓል መታሰቢያ በዓል በጅዳ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ቆንስላ ጽ/ቤት ተከበረ
 
                      127ኛው የአድዋ ድል በዓል መታሰቢያ ‹‹ዓድዋ፣ አንድነት፣ ጀግንነት፣ ጽናት›› በሚል መሪ ቃል በጅዳ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ቆንስላ ጽ/ቤት በፓናል ውይይት ተከብራል። በውይይቱ መክፈቻ የሚስዮኑ መሪ ክቡር አምባሳደር ሙሉጌታ ከሊል ንግግር የተደረገ ሲሆን፤ በዚህም ዓድዋ ኢትዮጵያ በወራሪው ፋሺስት ጣሊያን ላይ የተቀዳጀችው ድል ብቻ ሳይሆን ለመላው ዓለም ኢትዮጵያዊያን ለአገራቸው ሉዓላዊነት የፅናትና የቆራጥነት ተምሳሌት እንደሆኑ ያስመሰከሩበት ታላቅ ገድል መሆኑን አንስተዋል። በዕለቱም በተደረገው የፓናል ውይይት ላይም በዓሉን በማስመልከት የዓድዋ ጦርነት መንስኤ፣ ሂደት፣ ድል፣ ድህረ-ዓድዋም ድሉ ለመላው ዓለም ጥቁር ህዝቦች የነበረውን የጎላ ሚና ተወስቷል። አሁን ያለው ትውልድም የቀደመውን ደማቅ ወርቃማ ኅብረብሔራዊ ታሪኩን በመጠበቅ በቀጣይ የላቀ ድል ለማምጣት እንዲተጋ ተምሳሌትነቱ የላቀ እንደሆነም ተመላክቷል።
 
 
 
 
 
 
 

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram