የአፍሪካ ቀን በድምቀት ተከበረ

 
60ኛው የአፍሪካ ቀን ግንቦት 17 ቀን 2015 ዓ.ም በጅዳ ከተማ በደመቀ ሁኔታ ተክብሮ ውሏል፡፡ ፕሮግራሙ በጅዳ የሚገኙ የተለያዩ የአፍሪካ አገራት ቆንስላ ጽ/ቤቶች በጋራ ያዘጋጁት ሲሆን በበዓሉ ላይም ቆንስላ ፅ/ቤታችን ሀገራችንን በስፋት የሚያስተዋውቁ ስራዎችን አከናውኗል፡፡

በወቅቱም በጅዳ የኢትዮጵያ ኮሚውኒቲ ዓለምቀፍ ት/ቤት ተማሪዎች የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችን ባህል የሚያስተዋውቁ ውዝዋዜዎችን አቅርበዋል ፡፡ በበዓሉ ላይም የሳውዲ አረቢያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካ እና አካባቢው ቅርንጫፍ ከፍተኛ የመንግስ ባለስልጣናት እና የጅዳ እና አካባቢው ገዢ ተወካዮችም እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶች በእንግድነት ተገኝተዋል፡፡ በዓሉም የአፍሪካን ብዝሃነት ከማሳየቱም በተጨማሪ ተሳታፊዎች አገራቸውን የሚያስተዋውቁ ኢግዚብሽኖች አቅርበዋል ፡፡ ቆንስላ ጽ/ቤታችንም ከሀገራችን ባህላዊ እሴቶች ውስጥ የቡና አፈላል ስርአትን እና የተለያዩ ባህላዊ ምግቦችን በበዓሉ ላይ በማቅረብ ለታዳሚው የማስተዋወቅ ስራ ተሰርቷል፡፡
 

          

 

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram