በጄዳ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አመራሮች ምርጫ፤ በጄዳና አካባቢው የተለያዩ አደረጃጀቶች የተውጣጡ እጩ አመራሮች ሰኔ 09 ቀን 2015 ዓ.ም. በጄዳ ቆንስላ ጄነራል ጽ/ቤት በመገናኘት በቀጣይ ሁለት ዓመታት ኮሙኒቲውን የማስተባበር ሥራ የሚሰሩ ዘጠኝ አባላት ያሉት የሥራ አስፈፃሚ ምርጫ ተካሂዷል። በዚሁ መሰረት ከተለያዩ አደረጃጀቶች ተመርጠው ከመጡ 22 አባላት መካከል 9 የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ተመርጠዋል። ሥራ አስፈፃሚ አባላቱም ሰብሳቢ፣ ም/ሰብሳቢ፣ ፀሐፊ፣ ሂሳብ ሹም፣ ገንዘብ ያዥ፣ የማህበራዊ ጉዳይ ሃላፊ፣ የዜጐች ክትትል ሃላፊና ሁለት አባላት ያሉት የኢንስፔክሽን ኮሚቴ አባላት መርጠዋል። በዚሁ መሠረት አቶ ጀማል ዳዲ ሰብሳቢ፣ አቶ ሲይድ መሀመድም/ሰብሳቢ፣ አቶ መሀመድ ሲራጅ ፀሀፊ፣ ወ/ሮ ሙኒራ ጅሃር ሂሣብ ሹም፣ ወ/ሮ ሙሉወርቅ ነጋሽ ገንዘብ ያዥ፣ አቶ ፈሪድ ሸሪፍ ማህበራዊ ጉዳይ ሃላፊ፣ አቶ ሙሳ ሀሰን ዜጐች ክትትል ሃላፊ፣ አቶ ሚካኤል አጽበሃ የኢንሰፔክሽን ሰብሳቢ እና አቶ አብደላ አማን የኢንሰፔክሽን ፀሐፊ በመሆን ተመርጠዋል። 2 Post navigation በጄዳና አካባቢዋ ከሚኖሩ የተለያዩ የዳያስፖራ አደረጃጀት አመራሮች ጋር ውይይት ተካሄደ በክቡር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን አዘርባጃን ባኩ ከተማ