ክቡር አምባሳደር ሙሉጌታ ከሊል በጅዳ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ቆንስል ጄኔራል ከጅዳ ግዛት አስተዳዳሪ ልዑል ሳውድ ቢን ጃላዊ ጋር ተወያዩ፡-

============================
ክቡር አምባሳደር ሙሉጌታ ከሊል በጅዳ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ቆንስል ጄኔራል እ.ኤ.አ ሜይ 3 ቀን 2023 ዓ.ም ከጅዳ ከተማ አስተዳዳሪ ጋር ምክክር ያደረጉ ሲሆን በውይይታቸውም በኢትዮጵያ ስላሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች ሰፊ ገለጻ አድርገዋል።
ኢትዮጵያ በግብርና ምርቶች፣ በአበባ አትክልትና ፍራፍሬ፣ በታዳሽ ሃይልና በማዕድን ልማት፣ በስጋ ቆዳና የቆዳ ዉጤቶች፣ በጨርቃጨርቅና አልባሳት የኢንቨስትመንት መስኮች ሰፊ አቅም ያላት መሆኑን ያነሱት አምባሳደር ሙሉጌታ ከሊል የተለያየ የአየር ንብረት፣ የውሃ ሀብት፣ ሰፊ ገበያ የሚሆን የህዝብ ቁጥር እና አምራች የሆነ ወጣት ያለባት ሃገር መሆኗን ገልጸዋል። አያይዘውም መንግስት ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት የመሰረተ ልማትን በማሟላት የአንድ ማዕከል አገልግሎት የሚሰጡ የኢንደስትሪ ፓርኮች ማዘጋጀቱንም አምባሳደሩ አውስተዋል።
አስተዳዳሪ ልዑል ሳውድ ቢን ጃላዊ በበኩላቸው በሳውዲ ዓረቢያ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ታሪካዊ ግንኙነት ትልቅ ቦታ የሚሰጡት እንደሆነ በግዛታቸውም በርካታ ኢትዮጵያውያን ለዘመናት የሚኖሩ መሆናቸው የገለጹ ሲሆን ስለ ተሰጣቸዉ ገለፃ በማመስገን በቀጣይ በተጠቀሱት የኢንቨስትመንት መስኮች ለመሰማራት ፍላጎት ካላቸው የሳውዲ ባለሀብቶች ጋር በጽ/ቤታቸው በኩል እንደሚመለከቱት አረጋግጠዋል።

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook
YouTube
Instagram